ሐሰት: የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን እገዳ ውድቅ የሚያደርግ መግለጫ አላወጡም

በጃፓን መንግሥት ማህደር ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂድ ሱጋ አስተያየት ስለመስጠታቸው የሚያስረዳ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ፣ እንደነዚህ ያሉ መግለጫዎችን የሚያመለክቱ ምንም ዓይነት የዜና ዘገባዎችም የሉም ፡፡

PesaCheck
PesaCheck

--

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂድ ሱጋ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን እገዳ ውድቅ አድርገዋል የሚለው የፌስቡክ ልጥፍ ሐሰተኛ ነው።

በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “ጃፓን ከኢትዮጵያ እና ከተገፉት ወገኖች ጎን እንደምትሆን አረጋግጣለች ፡፡ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂድ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተገቢ አይደለም ሲሉ አልተቀበሉትም” ይላል ፡፡

ልጥፉ ላይ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር “ኢትዮጵያ በጠብ አጫሪነት አትታወቅም ፣ አገሪቷም ኃይልዋን ወደ ኮሪያ ፣ ኮንጎ ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን በመላክ ሰላም አስከባሪ መሆንዋን አሳይታለች” ሲሉ አክለዋል ይላል ፡፡

​​የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እ.ኤ.አ. ግንቦት 23 ቀን 2021 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በመጥቀስ ለኢትዮጵያ በሚሰጡት ኢኮኖሚያዊ እና ደህንነት ድጋፍ ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቀዋል ፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሳትፈዋል በተባሉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የአሜሪካ ቪዛ እገዳ መጣሉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያወጣው ጋዜጣዊ መግለጫም ያብራራል ፡፡ ይህ ልጥፍ ብቅ ያለው በዚህ አውድ ውስጥ ነው።

የኢትዮ-ጃፓን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እ.ኤ.አ.በ 1930 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ ኋላ ላይ በወዳጅነት እና የንግድ ስምምነት ሁለቱም አገራት አጠናክረውታል።

የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) እ.ኤ.አ. ከ 1972 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያን በልማትና በሰብዓዊ ዕርዳታ ዘርፎች እየደገፈ ነው ፡፡ የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ሰብዓዊ ዕርዳታ እ.ኤ.አ. በ 2020 ዓ.ም በሶስት እጥፍ አሳድጓል።

የጃፓኑ ጠ/ሚኒስትር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አልተቀበሉትም የሚለው ጽሁፍ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መድረኮች የሰጡትን ምላሽ ተከትሎ በፌስቡክ ተሰራጭቷል ፡፡

እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2021 ዓ.ም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰነችውን ውሳኔ ለመቃወም የመንግስት ደጋፊዎች ያደርጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል ፡፡

ምንም እንኳን ጃፓን እና ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቢኖራቸውም ጠ/ሚ ሱጋ የአሜሪካን ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ መጣሉን አልተቀበሉም የሚለው ወሬ መሠረተ ቢስ ነው ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሱጋ አሉ የተባለው መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የካቢኔዎቻቸው ኦፊሴላዊ ንግግሮች እና መግለጫዎች በሚሰራጭበት ኦፊሴላዊ ድረ ገጽ ላይ አይገኝም ፡፡

በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትር ሱጋ በኩል ተሰጥ​​ቷል የተባለውን መግለጫ በተመለከተ የታተመ የዜና ዘገባ የለም ፡፡

ፔሳቼክ የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺሂድ ሱጋ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን እገዳ ውድቅ አድርገዋል የሚለውን የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳ ቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::

እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሐሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::

በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::

ይህ የእውነታ ምርመራ በፔሳቼክ የእውነታ አጣሪ በቶሌራ ገምታ ተጽፎ በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔና በፔሳቼክ ዋና አዘጋጅ ሮዝ ሉካሎ አርትኦት፤ የቀረበ ነው::

እንዲሁም ከመጀመርያው እንግሊዝኛ ቋንቋ ዕትም በኋላ ለአማርኛ ቋንቋ ታዳሚዎች በሚስማማ መልኩ በኤደን ብርሃኔ ተተርጉሞ የቀረበ ነው።

አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::

ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው:: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::

Follow Us
Like Us
Email Us

ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::

--

--

Are they lying? Kenya’s 1st fact-checking initiative verifies statements by public figures. A @Code4Kenya and @IBP_Kenya initiative, supported by @Code4Africa.